በር:ፍልስፍና

ከውክፔዲያ


የፍልስፍና በር
በውክፔድያ የ ፍልስፍና
ጠቃሚ ዕውቀቶች ማከማቻ





መጻጽፍ · መደቦች · ፍልስፍና መዝገበ ቃላት በአማርኛ እንግሊዝኛ  · ተመራመር ይገኛል ቁም ነገር

ፍልስፍና

ፍልስፍና ከግሪኩ φιλοσοφία (ፊሎዞፊያ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የጥበብ ፍቅር ነው። ስለዚህ የፍልስፍና ዕውቀት ሁለት ነገሮችን መነሻ ያደረጋል። አንደኛው፣ «ጥበብ አለ» የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው «ይህ ጥበብ ሊደረስበት ይቻላል» የሚል ነው።

የየዘመኑ ሰዎች ጥበብ ላይ ለመድረስ ብዙ መንገዶችን ተጠቅመዋል። አንዳንዶች ሥነ ተረትን ሌሎች ሥነ ተማሎንና እንዲሁም ሥነ ዶግማን ሞክረዋል። ይሁንና እነዚህ አስተሳሰቦች ቁንጽል እውነታዎችን ከመያዝ ባለፈ ፍልስፍና ለመባል አልበቁም።

ፍልስፍናን ከላይ ከተገለጹት የዕውቀት ዘርፎች የሚለየው ዋናው ጉዳይ «አስተማማኝ እውቀትን» ለማግኘት መጣሩ ነው። ማናቸውም የፍልስፍና ዕውቀቶች ያለማቋረጥ ተጠርጥረው፣ ተመርምረውና ተተችተው ግን ፀንተው ሊቆሙ በቻሉ መሪ ሓሳቦች ይመሰረታሉ። ፍልስፍናን የመሪ ሓሳቦች ቁንጽል ስብስብ እንዳይሆን የሚያደርገው አመክንዮ ነው። መሰረታዊ ሃሳቦች በምክንየት ተያይዘው ሲዋቀሩ እና ሰፊ የዕውቀት ሥርዓት ሲገነባ ፍልስፍና ይባላል። በዚህ መንገድ ቁንጽል ሳይሆን ሰፊ፣ ተልካሻ ሳይሆን አስተማማኝ፣ የተነጣጠለ ሳይሆን ሥርዓታዊ ዕውቀት ይገኛል።

ጥገኛ አምክንዮ
ጥገኝነት የሚፋለሰው A እውነት ሆኖ B ውሸት ሲሆን ብቻና ብቻ ነው። ከላይ ባለው ቬን ምስል ይህ የውሸት ክፍል በነጭ ቀለም ተለይቶ ይታያል።
ጥገኝነት በሂሳብ ትርጓሜው እንዲህ ይሰፍራል

A → B ¬A B
የጥገኝነት አምክንዮን የሚተገብር የማብሪያ ማጥፊያ ትልም

ጥገኛ አምክንዮ በሁለት የአምክንዮ ዋጋወች የሚተገበር ሲሆን፣ ውጤቱ ውሸት የሚሆነው ቀዳሚ አረፍተ ነገሩ እውነት ሁኖ ተከታይ አረፍተ ነገሩ (ጥገኛ አረፍተ ነገሩ) ውሸት ሲሆን ብቻና ብቻ ነው። (ቀዳሚና ተከታይ አረፍተ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ከታች ሙሉ ማብራሪያ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ ) ከአምክንዮ አንጻር ጥገኛ አምክንዮ ከአይደለም....ወይም... ጋር እኩል ነው። በሂሳብ አጻጻፍ፣ p ቀዳሚ አረፍተ ነገር (አስጠጊ) ቢሆንና q ተከታይ (ጥገኛ) ቢሆን፣ የጥገኝነት ዝምድናቸው እንዲህ ይጻፋል p → q ፡ ሲነበብ p ስለዚህ q ነው። ይህ እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው ከ አይደለም p ወይም q ጋር ምንም ለውጥ የለውም። ይህን የመጨረሻውን ግኝት

በምሳሌ እንይ፡

መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ናት፣ ስለዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት

ከላይ በጻፍነው ትርጓሜ አንጻር ሲተረጎም

መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ አይደለችም ወይም መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት
ከላይ የተጻፉትን አረፍተ ነገሮች አነጻጽረው እኩለነታቸውን ያረጋግጡ

ይሕን ያውቁ ኖሯል፧...

የፍልስፍና የጥናት ዘርፎች

የተመረጠ ፈላስፋ 

ከፍልስፍና ቅርንጫፎች ጋር አጫጭር ትውውቅ

ፍልስፍና በተለያዩ ሰወች የተለያየ ግንዛቤና መረዳት አለው። ሆኖም ከሞላ ጎደል የፍልስፍና ዘርፎችና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንዲህ ይቀርባሉ፡
  • ሥነ ዲበ አካል : እውንነት ምንድን ነው? እውን የሆነ/የሆኑ ምን ነገሮች አሉ? ከምናስተውለው ዓለም ውጭ ሌላ ዓለም አለ?
  • ሥነ ዕውቀት: አለምን መረዳት እንችላለን? እንዴት ማወቅ እንችላለን? ከራሳችን ውጭ ሌላ ሃሳብ እንዳለ እንዴት እናውቃለን?
  • ሥነ ምግባር: ሰናይዕኩይ (ጥሩና መጥፎ) ልዩነት አላቸው? ካላቸው እንዴት ልንለያቸው እንችላለን? ምን አይነት ምግባር ሰናይ (ጥሩ) ነው? ለአንድ ምግባር ዋጋ ለመስጠት የዋጋ ስርዓት መኖር አለበት፣ ይህ የዋጋ ስርዓት ከየት ይመነጫል? ከአምላክ? ወይስ ከየት? አንድ ምግባር ፍጹም ጥሩ ወይም ፍጹም መጥፎ ሊባል ይችላል? የራበው ሰው ቢሰርቅ ስርቆቱ ዕኩይ ነው? ወይንስ ሥነ ምግባር አንጻራዊ ነው? እንዴት ህይወቴን መምራት አለብኝ? ሁላችንስ እንዴት እንኑር?
  • ሥነ አምክንዮ፡ ትክክለኛ ሃሳብ እንዴት እናመነጫለን? አንድ ሃሳብ ስሜት የማይሰጥ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የክርክርን አሸናፊ እንዴት መለየት ይቻላል?
  • ሥነ ውበት፡ ኪነት ምንድን ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት ቋሚ መስፈርት አለው? ኪነት መስፈርቱ ነው? እንግዲያስ የውበት ትርጉሙ ምንድን ነው? የኪነት አላማ ምንድን ነው? ኪነት እኛን እንዴት ይነካናል?ኪነት ዕኩይ ሊሆን ይችላል?ኪነት የህብረተሰብን ኑሮ ይሸረሽራል ወይስ ያሻሽላል? አንድ
  • ከዋኝ የሚሰራውን ያውቃል? ለምሳሌ ድራማ ላይ ፕሬዜዳንት የሆነ ከዋኒ ዕውን ፕሬዜዳንት ሆኖ ሊሰራ ይችላል? የኪነት ተግባር የውኑን አለም መኮረጅ ነው? በመኮረጁ የቱን ያክል ነባራዊውን አለም ያጣምማል?

የምዕራቡ አለም ፈላስፎች

ፍልስፍና ካሳለፈው ዘመን ብዛትና እንዲሁም ከጥናቱ ስፋት የተነሳ ብዙ ጊዜ በአንድ ሃሳብ ላይ የተለያዩ አቋሞች ይንጸባረቃሉ። ስለሆነም ፍልስፍናን በሃሳብ ደረጃ ከማጥናት ይልቅ "የዋና ዋናዎቹ ፈላስፋወች ሃሳብ ምን ነበር?" በማለት ማጥናት ሊቀል ይችላል። የሚቀጥሉት ሰዎች ከሞላ ጎደል ዋና ዋናወቹ የምዕራቡ አለም ፈላስፋወች ናቸው። እያንዳንዳቸው ለአሁኑ የምዕራቡ አለም ፍልስፍና ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል፦



ፓይታጎረስ


ሶቅራጠስ


ፕላቶ


አሪስጣጣሊስ


ሴኔካ


ኦግስጢን


አኩናስ


ደካርት


ሆብስ


ስፒኖዛ


ሎክ


ሌብኒዝ


ሁም


ካንት


ቤንታም


ሄግል


ሾፐናውር


ኬርክጋርድ


ማርክስ


ኒሺ


ኸስረል


ሄድጋ


ሳትራ


ማካቬሊ